ፒያሳ ላይ

ሮፍናን

ነፀብራቅ
ትዝ ይለኛል እንደ ትላንት
የመጀመሪያ ቀን ሳያት
ያኔ የቬል ሱሪው ነገር
አፍሮ ብጥር ብጥር ብጥር

ከአዲስ ከተማ በቶሎ
አይ በቶሎ
ጎዞዬ ቤቴ አራት ኪሎ
አይ አራት ኪሎ
ልጅት ነች ከናዝሬት ስኩል
ናዝሬት ስኩል
ነገሯ በአራዳ በኩል

በግርግሩ መሀል ተያየን
አኔ እና እሷ ያኔ ተገናኘን
ፒያሳ ላይ 
ፒያሳ ላይ
ትዝ ይለኛል አይኔ ከአይንሽ
መጀመሪያ ስተዋወቅሽ
ፒያሳ ላይ 
ፒያሳ ላይ
ታሪክ ያለው እጅ ወደላይ

አዲስ አበባን
ሳያት ሰባዎቹ መሀል
ትዝ ይለኛል ብዙ ነገር
ሮሀና የአንቺ ፍቅር
አባትሽ ያ ጀነራል
ያ ጀነራል
አስረው ሲገርፉ ወንድሜን
ወነድሜን ወንድሜን
እኔ እና አንቺ ግን አልፈናል
አው አልፈናል
ፍቅርን በባለአንጣዎች መሀል
አዬ አዬ
አስታውሳለው መፅሀፍቶቹን
ሳመጣልሽ የሀዲስ በአሉ ሎሬት ፀጋዬን
ከአራዳው ስር ብለን ተቀጣጥረን
አውቶቢሷ ሳትመጣ በእግሬ እቀድማት ነበር

በግርግሩ መሀል ላይሽ
ከራዳው ስር አንቺን ላገኝሽ
ፒያሳ ላይ 
ፒያሳ ላይ
አይረሳም የጥንቱ ነገር
ያሳለፍነው ከደጉ መንደር
ፒያሳ ላይ 
ፒያሳ ላይ
ታሪክ ያለው እጅ ወደላይ

ጨዋታ ጨዋታ ከአራዳው ቦታ
ጨዋታ ጨዋታ ከአራዳው ቦታ
ሳሚልኝ ቤቱን ጊዮርጊስን አዬ
ሳሚልኝ ቤቱን ጊዮርጊስን አዬ
ጥምቀት ነው ጨዋታ ከአራዳው ቦታ
ጥምቀት ነው ጨዋታ ከአራዳው ቦታ
ሸኘው ታቦቱን አድዋ ዘማቹን አዬ 
ሸኘው ታቦቱን አድዋ ዘማቹን አዬ
ዘራፍ ዘራፍ ዘራፍ
አስተያየቶች (0)