የሰው ቅኔ

ሮፍናን

ነፀብራቅ
ብዬሻ ለኔ እያለሽ ከኔ
ለካስ ሁለት ፊት ነሽ
የሰው ቅኔ
የማየው የዋህ እርግብ መልክሽ
ፍቅር ጋርዶብኝ መብረርሽን

አዬዬዬዬዬ
ብላቴናው ኖረ ሲታገስ
አዬዬዬዬዬ
ሰምና ወርቅ እስኪለይ ድረስ
አዬዬዬዬዬ
ይብላኝ ለዘረፈሽ ከኔ
አዬዬዬዬዬ
የፈታሁሽ የሰው ቅኔ

ተው ምነው ክራሬ ተው ምነው
ከድታህ የሄደችን ታመጣለህ ምነው

ጀምረን ነበረ ፍቅርን እንደ ድውር
የጥጥ ቃላት ክምር በቀናቶች ዝውር
ጥለቱን በመልኳ አሳምሬ ነድፌው
ቋጪው ብላት እምቢ ብቻዬን ጠልፌው

አባይን ብከተል ሰጠኝ ለፈርሆን
መጨረሻው ሀዘን ያንቺ አፍቃሪ መሆን
እራሴን ከልቤ አጣልተሸብኝ
ሰው አልሆንም ነበር እሱ ባያየኝ

አዬዬዬዬዬ
ብላቴናው ኖረ ሲታገስ
አዬዬዬዬዬ
ሰምና ወርቅ እስኪለይ ድረስ
አዬዬዬዬዬ
ይብላኝ ለዘረፈሽ ከኔ
አዬዬዬዬዬ
የፈታሁሽ የሰው ቅኔ

ጀምረን ነበረ ፍቅርን ማሾር እንደ ድውር
ፈትለን ነበር ቀጭን ፍቅር በቃላቶች ዝውር
ጥለቱን ልክ እንደ መልኳ አሳምሬ ነድፌው
ቋጪው ብላት እምቢ ብቻዬን ጠልፌው
አይ ብታይው ማማሩን ድንቁን ስራዬን
ከኔ የዘረፈሽ መቼም የማይሰጥሽን
ብቻዬን ጠልፌ ላንቺ የሰራሁትን ሸማ
ላደላት አስቀመጥኩላት ከላቋጨውማ
ሀ ግዕዝ ሁ ካዕብ ብሎ ህ ሳድስን አስከትሎ
አስከትሎን አስከትሎ
የጀመረው በአቦጊዳ
ለፍቅር ነበር እንግዳ
አይ እንግዳን አይ እንግዳ
ብላቴናው ኖረ ሲታገስ ቅኔ እስኪገባው ድረስ
ድረስ
ኤኤ
ድረስ
ወርቁን ያገኘው እለት ያኔ
ፈታሁሻ የሰው ቅኔ

ትዝታዬን ትቼ ቅኝት ሌላ ህይወት ሀሁ እንደገና
ትዝታዬን ትቼ ቅኝት ሌላ እያየሁሽ ወደ ኋላ
ትዝታዬን ትቼ ቅኝት ሌላ ህይወት ሀሁ እንደገና
ትዝታዬን ትቼ ቅኝት ሌላ የፊቴን ላይ ግድ ነውና
አስተያየቶች (0)