ይድረስ ለምውደሽ
እጅግ ለምታምሪው
ይድረስ ላይኔ ቆንጆ
ይህን ለምትሰሚው
የውስጤን በደብዳቤ
እንዲ ብዬ ፃፍኩት
ፖስታውን ትቼ ብዜማዬ አሽኩት

ከአልማዝ ከእንቁ በላይ
መልክቴ ይበልጣል
ወረቀት ተቀዳጀ ነው
እንዴት ይታመናል
ስለዚህ ደብዳቤ
ጽፌ እንደጨረስኩት
ፖስታውን ተውኩና
በሙዚቃው ላኩት

ሰው የለም እንዳንቺ
ልቤ የወደደው
ሲነጋም ሲመሽም
አንቺን ነው ማስበው
እውነትን ሳልናገር
ሁሌ ከምትርቂኝ
እንገዲ ጠብቃለሁ
ምን እንደምትዪኝ

ይድረስ ለኔ ቆነጆ
ይድረስ ለኔ ቆነጆ
ይድረስ ለኔ ውብ
ሳይሽ ዋልኩና
አደርኩኝ ሳልም
ማየቱስ ምን ሊያድርግልኝ
ማለሙም ትርፍ የለው
ባገኝሽ ነው እንጂ
ልቤን የውነት ደስ የሚለው

እንዳልኩሽ መልክቴ
ከአልማዝ ይበልጣል
የፍቅር ቃላት በምን
ዋጋው ይተመናል
ስለዚ ደብዳቤን
ጽፌ እንደጨረስኩት
ፖስታውን ተውኩና
በሙዚቃ ላኩት

ሰው የለም እንዳንቺ
ልቤ የወደደው
ሲነጋም ሲመሽም
አንቺን ነው ማስበው
እውነትን ሳልናገር
ሁሌ ከምትርቂኝ
እንገዲ ጠብቃለው
ምን እንደምትዪኝ

ናናና
አማሌ ሌሌሌሌሌሌሌ ና ናዬ
ናናና
መልሱን ልከሽልኝ
ልዳነው ከስቃዬ
ናናና
ሽኮሪና ናናናናናናዬ
ናናና
ደብዳቤዬን ላኩት
በዚ ሙዚቃዬ
ናናና

ሰው የለም እንዳንቺ
ልቤ የወደደው
ሲነጋም ሲመሽም
አንቺን ነው ማስበው
እውነትን ሳልናገር
ሁሌ ከምትርቂኝ
እንገዲ ጠብቃለው
ምን እንደምትዪኝ
አስተያየቶች (0)