በሰባ ደረጃ

ቴዲ አፍሮ

ከመኮንን ድልድይ ከንጨት ፎቁ በላይ
ሲመሽ እንገናኝ
መጣሁ አንችን ብዬ ሳይከብደኝ እርምጃው
በሰባ ደረጃው

በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃው በፒያሳ አርጌ
በፍቅር ማነቂያው ዶሮ እንዳይል በከንቱ እሪ አንችን ወዶ
ክራሩን ስትሰሚ ብቅ በይ ቆሚያለሁ ከበርሽ ማዶ

ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
ሲመሽ ወደ  ማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ

ማታ ማታ ማታ ማታ
ማታ ማታ ማታ ማታ
ማታ ማታ ማታ ማታ
ማታ ማታ ማታ ማታ

ማታ ማታ
አምጧት ከጎኔ ትቀመጥ
እንጀራ አይቀርብም ካለወጥ
አቅፎ ገላዋን አልጠግብ ያለው
ማነው ካላችሁ ማነው ማነው

ልቤ ልቤ ነው ልቤ ራብተኛው
ልቤ ልቤ ነው ልቤ ራብተኛው
እሷን ወዶ ሌት የማይተኛው
እሷን ወዶ ሌት የማይተኛው
ይውጣ ይውጣ እግሬ ይዛል በርምጃው
ይውጣ ይውጣ እግሬ ይዛል በርምጃው
ከሷ አይብስም ሰባ ደረጃው
ከሷ አይብስም ሰባ ደረጃው

ዎይ ዘበናይ ነይ ዘበናይ
ዘበናይ ዘበናይ

ሲመሽ ወደማታ
ሁሉ ዘግቶ በሩን
ታም ታራም ሳረገው
ብቅ በይ ክራሩን
ታም ታራራም ታራራም ታራራም
ሳረገው ክራሩን
ታም ታራራም ታራራም ታራራም

ፀጉሯን ተተኩሳው እንዳርምዴ ሜሪ
ዘበናይ ናት ፍቅሯን በክራር ነጋሪ
ታም ታራራም ታራራም ታራራም
በክራር ነጋሪ
ታም ታራራም ታራራም ታራራም

ሄዶ ከኮሪያ ዘማች ሲመለስ
ዘማች ሲመለስ
ያውሳል ናፍቆቱን በክራሩ ድምፅ
በክራሩ ድምፅ
ፍቅርሽ አስጨንቆ መላዎስ አቃተኝ
መላዎስ አቃተኝ 
አሀሀ
ተደናበርኩልሽ ጥይት እንደሳተኝ
ጥይት እንደሳተኝ
ሳተና ነበርኩኝ ተኳሽ በመውዘሬ
ተኳሽ በመውዘሬ
ለዘበናይ ብቻ እጄን ሰጠሁ ዛሬ
እጄን ሰጠሁ ዛሬ
ዎይ ዘበናይ ነይ ዘበናይ
ዘበናይ ዘበናይ

አሀ አሀ አሀ አሀ

በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃው በፒያሳ አርጌ
እንዳውራ ዶሮ ክንፍ ኮቴን እየሳብኩት መሬት ለመሬት
በዞርኩት ገላሽን ሳትወጣብኝ ፀሀይ ሳይነጋብኝ ሌት
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ

ማታ ማታ ማታ ማታ
ማታ ማታ ማታ ማታ
ማታ ማታ ማታ ማታ
ማታ ማታ ማታ ማታ
ማታ ማታ

ሞልቶ ባራዳ ያርመን ዳቦ
ሳሳ አከላቴ ሰው ተርቦ
አቅፎ ገላዋን አልጠግብ ያለው
ማነው ካላችሁ ማነው ማነው

ልቤ ልቤ ነው ልቤ ራሃብተኛው
ልቤ ልቤ ነው ልቤ ራሃብተኛው
እሷን ወዶ ሌት እማይተኛው
እሷን ወዶ ሌት እማይተኛው
ይውጣ ይውጣ እግሬ ይዛል በርምጃው
ይውጣ ይውጣ እግሬ ይዛል በርምጃው
ከሷ አይብስም ሰባ ደረጃው
ከሷ አይብስም ሰባ ደረጃው

ዎይ ዘበናይ ነይ ዘበናይ
ዘበናይ ዘበናይ
አረረ
 
አይወጣም ደረጃ ቢፈጥን ሴሸኝቶ 
እንደኔ ካልሄደ በፍቅር ተገፍቶ 

ታም ታራራም ታራራም ታራራም
በፍቅር ተገፍቶ
ታም-ታራራም ታራራም ታራራም
መድፈሪያሽ ወርቅ ነው
ብርም አይገዛሽ
ልብ የሌለው ሀብል ግድም አይሰጥሽ
ኬረዳሽ
ታም ታራራም ታራራም ታራራም
ግድም አይሰጥሽ
ታም ታራራም ታራራም ታራራም

ካንገትሽ ላይ አርጊኝ እንደማር ተሬዛ
እንደማር ተሬዛ
ወዲህ ወዲያ እንዳልል አደብ እንድገዛ
አደብ እንድገዛ
ተከለከለ አሉ የንጉስ አዳራሽ
የንጉስ አዳራሽ
የክት ያለበሰ አይገባም በጭራሽ
አይገባም በጭራሽ
መጣሁ ከኮሪያ ይዤልሽ ሰኣት
ይዤልሽ ሰኣት
በፓሪ ሞድሽ ላይ አምረሽ ታይበት
አምረሽ ታይበት

ዎይ ዘበናይ ነይ ዘበናይ
ዘበናይ ዘበናይ

ሰናይ እናናዬ 
ተይ አሁን ነይ
አሁን ነይ
ሰናይ እናናዬ 
ተይ አሁን ነይ
አሁን ነይ አሁን ነይ
ሰናይ እናናዬ 
ተይ አሁን ነይ
አሁን ነይ አሁን ነይ
ሰናይ እናናዬ 
ተይ አሁን ነይ
አሁን ነይ አሁን ነይ
አስተያየቶች (0)

ለእርስዎ የምንመርጠው

የበሰባ ደረጃ ዘፈን ዝርዝር መረጃ

ዘፋኝ
ጸሐፊ
ቋንቋ
አማርኛ