ያኔ አልሻም ብሎ ትቶ የሄደውን
አሁን ነይ ይለኛል ስሙልኝ ቀልዱን
ያኔ አልሻም ብሎ ትቶ የሄደውን
አሁን ነይ ይለኛል ስሙልኝ ቀልዱን
ቆይ አንተስ ብትሆን
ወደኔ ሚያመጣህ ምን ተገኘ አሁን
ስንሰፈሰፍ የኮራኸው
ስንገበገብ የጠፋኸው

ባንቺ ያረኩት በርግጥ አልፎ እኔንም ያመኛል
ጭንቅ ነው ሳስታውስ መች ሀሳብ ያርፍልኛል
ሳያይ ያለፈው አይኔ ሀሳብ ፍቅርሽ ደብዝዞ
በአጀባ ሰክሮ ነው በጭብጨባ ደንዝዞ

በዝቶ አሟቂ ቃሌን አይንም ሆኖ በኔ ላይ
ቀልቤ የትም አደረ ለመደ የልብ አከራይ
አለው አለውም ባይ ላይበጀኝ ሊሄድ ትቶ
እንቅፋት አበዛ እግሬ እዚም እዛም ረግጦ
ደሞ ሰማው ብለሻል የሱ መሆን ንዴት ትርፉ
ነክሰው ተፍተውኛል ጓደኞችሽ ብለው ክፉ
ስሜ ነው አውቃለው ሁሉን አብራሪ በክንፉ
በልጅነት ዘመን ነው ሳይገባኝ ህይወት ቁልፉ
አብሮነትሽ ናፍቆኛል ዋጋው ገብቶኛልና
ይቅር በይ ተቀበይኝ ካልወሰደሽ ሰው ሌላ
አሁን ሄጃለው
ቃል ካልሰጠሽ መሀላ አስቢ ጠብቃለው
ረስቼሀለው
እንደ አዲስ ተዋወቂኝ ሌላ ሰውም ሆኛለው
አሁን ሄጃለው
ቃል ካልሰጠሽ መሀላ አስቢ ጠብቃለው
ረስቼሀለው
እንደ አዲስ ተዋወቂኝ ሌላ ሰውም ሆኛለው

ያኔ አልሻም ብሎ ትቶ የሄደውን
አሁን ነይ ይለኛል ስሙልኝ ቀልዱን
ያኔ አልሻም ብሎ ትቶ የሄደውን
አሁን ነይ ይለኛል ስሙልኝ ቀልዱን
ቆይ አንተስ ብትሆን
ወደኔ ሚያመጣህ ምን ተገኘ አሁን
ስንሰፈሰፍ የኮራኸው
ስንገበገብ የጠፋኸው

ዕድል ጥሎ ሲሄድ መች ያስታውቃል
ሲያልፍ እንደማይቆጭ ሲያመልጥም ያሳስቃል
ሁሌ ያለ ይመስላል ሲመጣ ባንዴ በዝቶ
አልፎም ባይገባ ከሚያቃጥል ዘግይቶ

ደሞ ሰማው ብለሻል የሱ መሆን ንዴት ትርፉ
ነክሰው ተፍተውኛል ጓደኞችሽ ብለው ክፉ
ስሜ ነው አውቃለው ሁሉን አብራሪ በክንፉ
በልጅነት ዘመን ነው ሳይገባኝ ህይወት ቁልፉ

አብሮነትሽ ናፍቆኛል ዋጋው ገብቶኛልና
ይቅር በይ ተቀበይኝ ካልወሰደሽ ሰው ሌላ
አሁን ሄጃለው
ቃል ካልሰጠሽ መሀላ አስቢ ጠብቃለው
ረስቼሀለው
እንደ አዲስ ተዋወቂኝ ሌላ ሰውም ሆኛለው
አሁን ሄጃለው
ቃል ካልሰጠሽ መሀላ አስቢ ጠብቃለው
ረስቼሀለው
እንደ አዲስ ተዋወቂኝ ሌላ ሰውም ሆኛለው
አሁን ሄጃለው
ቃል ካልሰጠሽ መሀላ አስቢ ጠብቃለው
ረስቼሀለው
እንደ አዲስ ተዋወቂኝ ሌላ ሰውም ሆኛለው
አስተያየቶች (0)