ምርጫ አላት

ዮሐና

ዮሐና
እቴሜቴ አንቺ የሎሚ ሽታ
ልውሰድሽ ቢላት ሰውየው ማታ
አለፈች እንዳልሰማ
ልቧ ከዛ የለማ

እቴሜቴ አንቺ የሎሚ ሽታ
ልውሰድሽ ቢላት ሰውየው ማታ
ምን ሊውል ቢምልላት
ወይ ፍንክች እንዳለች ናት

አይ 
ካልወደደች አትነካም
ትርፉ ንዴት 
ትርፉ ድካም
ጠብ የማይል ውበት
ኩሩ ልብ ሰቷታል

ንቃለች የኔ ፋንታ
በሰው ሀይል አትረታም
ወዳ ካየች 
ለሊት ቀን ያንሳታል

ልጅት ምርጫ አላት
ምርጫ አላት
ልጅት ምርጫ አላት
ምርጫ አላት
ልጅት ምርጫ አላት
ምርጫ አላት
ልጅት ምርጫ አላት
ምርጫ አላት

እቴሜቴ አንቺ የሎሚ ሽታ
ልውሰድሽ ባይሆን ሸንጋዩን ትታ
ፍላጎቷን ብቻ አይታ
አረፈች እጄ ገብታ

እቴሜቴ አንቺ የሎሚ ሽታ
አርፋለች በራ ጎጆዋን አግኝታ
ልብ የሌለው የሚገዛት
እሷስ መች የዋዛ ናት

አይ 
ካልወደደች አትነካም
ትርፉ ንዴት 
ትርፉ ድካም
ጠብ የማይል ውበት
ኩሩ ልብ ሰቷታል

ንቃለች የኔ ፋንታ
በሰው ሀይል አትረታም
ወዳ ካየች 
ለሊት ቀን ያንሳታል

ልጅት ምርጫ አላት
ምርጫ አላት
ልጅት ምርጫ አላት
ምርጫ አላት
ልጅት ምርጫ አላት
ምርጫ አላት
ልጅት ምርጫ አላት
ምርጫ አላት

አይ ካልወደደች አትነካም
ትርፉ ንዴት ትርፉ ድካም
ጠብ የማይል ውበት
ኩሩ ልብ ሰቷታል
ንቃለች የኔ ፋንታ
በሰው ሀይል አትረታም
ወዳ ካየች ለሊት ቀን ያንሳታል

ልጅት ምርጫ አላት
ምርጫ አላት
ልጅት ምርጫ አላት
ምርጫ አላት
ልጅት ምርጫ አላት
ምርጫ አላት
ልጅት ምርጫ አላት
ምርጫ አላት
አስተያየቶች (0)