ሳቅሽ ይጎዳል

ዮሐና

እረፍት
ተቆጪኝ... እሱ ይሻላል
ተቆጪ... ኝ እሱ ይሻላል
ተቆጪኝ... እሱ ይሻላል
ተቆጪ... ኝ እሱ ይሻላል

እውነቱን አውቀሻል ውሸቴም ገብቶሻል
ባይታይ ከፊትሽ
እንዳወኩ አውቀሻል ከፊቴ ይታይሻል
ባይጠይቅ አፍሽ
ምሬቱን አውቀሻል ውሸቴም ገብቶሻል
ባይታይ ከፊትሽ
እንዳወኩ አውቀሻል ከፊቴ ይታይሻል
ባይጠይቅ አፍሽ

ደፍሬ እንዳልጠይቅሽ እኔ ይቅርታ
ምንብዬ ግን ልጀምረው
ይሸፈናል ውሸት ብዬ ቀባጠርኩኝ
ሀጥያቴን አመረርኩኝ
አላውቅም ደብቄሽ ፍፅሞ እመኚኝ
ዋሽቼም ከዚህ በቀር
ዘላበድኩ እውነቱን እንደማትረጂኝ
ሲያዝብኝ በራሴው ሳከር

አንቺ ግን እንዳልሰማ አይተሽ ሁሉን እንዳላየ
እንዳልገባው ክፉ ደግ እንዳላየ
ሰላም ሆንሽ ፀብ ይሁን እርቅም ባላየ
ናፈኩት ቁጣሽ ዘገየ

ሳቅሽ ይጎዳል ልቆ ቁጣሽን
ማለፍሽ ጎዳኝ ከፍጥጫሽ
ሳቅሽ ይጎዳል ልቆ ቁጣሽን
ማለፍሽ ጎዳኝ ከፍጥጫሽ

ተቆጪኝ... እሱ ይሻላል
ተቆጪ... ኝ እሱ ይሻላል
ተቆጪኝ... እሱ ይሻላል
ተቆጪ... ኝ እሱ ይሻላል

እውነቱን አውቀሻል ውሸቴም ገብቶሻል
ባይታይ ከፊትሽ
እንዳወኩ አውቀሻል ከፊቴ ይታይሻል
ባይጠይቅ አፍሽ
ምሬቱን አውቀሻል ውሸቴም ገብቶሻል
ባይታይ ከፊትሽ
እንዳወኩ አውቀሻል ከፊቴ ይታይሻል
ባይጠይቅ አፍሽ

ፈራሁኝ ቅር አለኝ ፍቅርሽ ትዝ እያለኝ
ውስጥሽም የገፋኝ የጠላኝ መሰለኝ
ስንት ያልኩለት ፍቅር ብዙም የቀየረኝ
ሆድ ባሰኝ በእጄ የገደልኩት መሰለኝ

አንቺ ግን እንዳልሰማ አይተሽ ሁሉን እንዳላየ
እንዳልገባው ክፉ ደግ እንዳላየ
ሰላም ሆንሽ ፀብ ይሁን እርቅም ባላየ
ናፈኩት ቁጣሽ ዘገየ

ሳቅሽ ይጎዳል ልቆ ቁጣሽን
ማለፍሽ ጎዳኝ ከፍጥጫሽ
ሳቅሽ ይጎዳል ልቆ ቁጣሽን
ማለፍሽ ጎዳኝ ከፍጥጫሽ

ተቆጪኝ... እሱ ይሻላል
ተቆጪ... ኝ እሱ ይሻላል
ተቆጪኝ... እሱ ይሻላል
ተቆጪ... ኝ እሱ ይሻላል

ሳቅሽ ይጎዳል ልቆ ቁጣሽን
ማለፍሽ ጎዳኝ ከፍጥጫሽ
ሳቅሽ ይጎዳል ልቆ ቁጣሽን
ማለፍሽ ጎዳኝ ከፍጥጫሽ
አስተያየቶች (0)